Logic and Critical Thinking

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 14

JOIN @Aplustutorialofficial

LOGIC AND CRITICAL THINKING

Chapter One Exercise Questions With Their


Respective Explained Answer

DIRECTION : THERE ARE A TOTAL OF 32


QUESTIONS WITH TRUE OR FALSE, MULTIPLE
CHOICE AND MATCHING ITEMS. THE ANSWER FOR
EACH QUESTION IS BRIEFLY EXPLAINED IN A
WELL UNDERSTANDABLE MANNER WHICH IS
SUPPOSED TO SUPPORT STUDENTS IN A HEAD OF
BEING COMPATIBLE WITH UNIVERSITY EXAMS.
ALL QUESTIONS ARE BUNDLED FROM CHAPTER
ONE THAT KEEP UP WITH STANDARD OF
ETHIOPIAN UNIVERSITY.

© This file is ultimately prepared by A+ Tutorial Class, a well known and


indispensable tutorial for first year university students.

Register @Aplustutoriallbot
JOIN @Aplustutorialofficial

Part I : Say True if the statement is correct and False if the


statement is incorrect.
1) According to Skeptics, any search for truth is futile because truth can not be
attained.

1ኛ) ጥያቄው የሚለው: እንደ skepticism አመለካከት ፥ እውነትን ለማግኘት የሚደረግ ማንኛውም ፍለጋ ፍሬ ቢስ ከንቱ
ድካም(futile) ነው። ምክንያቱም እውነት ሊደረስበት የማይቻል ነገር ነው።

☼ Explanation: ከ ፍልስፍና ክፍሎች አንዱ የሆነው Epistemology መሰረታዊ ስለሆኑ ጉዳዮች(fundamental


issues) መልስ ለማግኘት ፍለጋ ያደርጋል። ከፍለጋዎቹ አንዱ "እውነት(truth) ን ማግኘት ይቻላል ወይ❓" የሚል ነው።
በዚህ ጉዳይ ላይ skepticism የተባለው ቲዎሪ የራሱን መላምት አስቀምጧል። skepticism ማለት መጠራጠር ፤ እርግጠኛ
አለመሆን ማለት ነው። እንደ skepticism አመለካከት "የሰው ልጆች 100% የተረጋገጠ ፥ ሊታመን የሚችል(አስተማማኝ)
የሆነ ዕውነት ላይ ሊደርሱ አይችሉም ፤ ዕውነትን ለማግኘት የሚደረግ ማንኛውም ፍለጋ ግብዝነት(vain) ና ከንቱ ድካም ነው"
ይላል። ሰዎች አስተማማኝ የሆነ ዕውነት ና ዕውቀት ላይ ለምን መድረስ እንዳልቻሉ skepticism የራሱን ምክንያቶች
አስቀምጧል። ሞጁላችሁ ላይ ወይም ቲቶርያሉ ላይ ማንበብ ትችላላችሁ ፤ ስለዚህ መልሱ True ነው ማለት ነው።

✅ Answer : True

2) searching for meaning and rational basis for moral judgement and principles
is the business of normative ethics.

2ኛ) ጥያቄው የሚለው: የሰው ልጅ ለሚያርጋቸው ድርጊቶች ሞራላዊነት ና የሰው ልጅ ለሚያወጣቸው መርሆዎች
የሚያጠናው Ethics ነው። ታዲያ በ Ethics ውስጥ ያሉ ቃላቶች(ethical terms) ን ትርጉም የሚያጠናው Normative
Ethics ነው።

☼ Explanation: ከፍልስፍና ክፍሎች አንዱ Axiology ነው። Axiology ስለ ዋጋ ፥ እሴት(value) የሚያጠና


የፍልስፍና ክፍል ነው። በ axiology ትምህርት ዋጋ(value) ማለት በብር ና በቁስ የሚተመነውን ዋጋ አይደለም። ለምሳሌ
የእናንተ ስልክ ዋጋ(value) አለው ፤ በብር የሚተመን ዋጋ። ስለዚህ axiology ስለ ስልካችሁ አያጠናም። ይልቁንም
Axiology በብር ወይም በቁስ ስለማይተመኑት ፤ ስለ ስነ-ምግባራዊ ፥ ማህበረሰባዊ ና ፖለቲካዊ እሴቶች ወይም ዋጋ
የሚያጠና ነው። ታዲያ Axiology በሶስት ይከፈላል። እነርሱም

• Ethics - የሰው ልጆች ስለሚያደርጓቸው ድርጊቶች ትክክለኛነት ወይም ስህተትነት የሚያጠና ነው።
Aesthetics - ስለ ውበት(beauty) ና ከውበት ጋ ስለተያያዙ ጉዳዮች የሚጠና ነው።
Social and political philosophy - ማህበረሰብ ና ፖለቲካ ያላቸውን ቁርኝነት የሚያጠና ነው።Ethics ደግሞ በሶስት
ይከፈላል። እነርሱም
► Normative Ethics - የሰው ልጆች የሚያደርጋቸው ድርጊቶቹን ፥ ተግባሩን ና ውሳኔዎቹን ለመገምገም ና
ለመዳኘት የሞራል ህጎችን ና መርሆዎችን የሚያጠና ነው። በሌላ አባባል የትኛው ድርጊት ትክክል ነው ፥ የትኛው ድርጊት
ስህተት ነው የሚለውን በሳይንሳዊ መንገድ የሚያጠና ነው።
► Non-normative Ethics(Meta-Ethics) - ስለ ስነ-ምግባራዊ ቃላቶች(ethical terms) ነው
የሚያጠናው። what is "good"? What is "bad"? What is "right"? What is "wrong"? የነዚህን ና
ሌሎች የስነ-ምግባር ቃላቶችን ትርጉም ነው የሚያጠናው።
► Applied Ethics ደግሞ አወዛጋቢ(controversial) ስለሆኑ ጉዳዮች ነው የሚያጠናው።
ስለዚህ ስለ ስነ-ምግባራዊ ቃላቶች(ethical terms) የሚያጠናው Non-normative(meta-ethics) ነው እንጂ
normative Ethics አይደለም። ስለዚህ መልሱ false ይሆናል ማለት ነው።

✅ Answer : False

Register @Aplustutoriallbot
JOIN @Aplustutorialofficial

3) The value of philosophy depends not on direct utility of tangible aspects but
on indirect implications in assisting the mind to think critically.

3ኛ) ጥያቄው የሚለው: የፍልስፍና ጥቅሙ የሚታይ የሚዳሰሱ አለማዊ ና ስጋዊ ቁሶችን ለሰዎች ለመስጠት አይደለም ፤
ይልቁንም የሰው ልጆች ከግብዝነት በፀዳ መልኩ ስለ ተፈጠሩባት አለም ምንክንያታዊ አስተሳሰብን ለሰው ልጆች ለማላበስ ነው።

☼ Explanation: ፍልስፍና የሰው ልጆች ስለ universe ና በ universe ውስጥ ስላሉት ነገሮች በ መደነቅ በመገረም ፤
ጥያቄን መጠዬቅ ፤ የተሻለ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ በፍለጋ መኳተን ፤ በምክንያታዊነት ነገሮችን ማሰስ ና መመልከት ነው።
ስለዚህ ፍልስፍና የሰው ልጆች ስለሚኖሩባት አለም ምክንያታዊ አመለካከት ና አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ያስችላቸዋል እንጂ
እንዴት ሀብታም መሆን እንዳለባቸው ና እንዴት የተመቻቸ ኑሮ መኖር እንዳለባቸው አያስገነዝብም። ስለዚህ መልሱ True
ነው።

✅ Answer : True

4) The critical task of philosophy is providing a defensive answer to a certain


question or answer.

4ኛ) ጥያቄው የሚለው: የፍልስፍና ዋና ተግባሩ ለሆነ ጥያቄ ወይም በአንድ ጉዳይ ላይ ለሚነሳ ጥያቄ ማረጋገጫ መልስ መስጠት
ነው።

☼ Explanation ፡ በመሰረቱ ፍልስፍና በሆነ ጉዳይ ላይ ለሚነሳ ጥያቄ ማረጋገጫ ወይም መልስ መስጠት አይችልም።
ምክንያቱም ፍልስፍና በ Experiment የተደገፈ ሳይንስ አይደለም። የፍልስፍና ዋና አላማም መልስ መስጠት አይደለም።
ይልቁንም ፍልስፍና መሰረታዊ ስለሆኑ ስለ ሰው ልጆች ጉዳዮች ና መስተጋብሮች ፥ ስለ universe ፥ ስለ ፈጣሪ ወዘተ ጥያቄን
ማንሳት ና በጉዳዩ ላይ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ሀሳቦችን እያነሱ መወያዬት ና የራሰን ምልከታ ማንፀባረቅ ነው። የ ኮረና በሽታ
መንስኤው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ፍልስፍና defenesive answer(ማረጋገጫ መልስ) አይሰጥም። ለዚህ
defensive answer ሊሰጥ የሚችለው የህክምና ሳይንስ ነው ፥ እርሱም በርካታ experiment በመስራት ፥ sample
በመውሰድ ና በማጥናት። ስለዚህ ፍልስፍና በሆነ ጉዳይ ላይ ለሚነሳ ጥያቄ ትክክለኛ ና የተረጋገጠ መልስ መስጠት ስራው
አይደለም። ስለዚህ መልሱ False ነው።

✅ Answer : False

5) Empiricism claims that reason is the source of knowledge.

5ኛ) ጥያቄው የሚለው: ምክንያታዊነት(reason) የእውቀት ምንጭ ነው ይላል Empiricism።

☼ Explanation : ከአራቱ የፍልስፍና ክፍሎች አንዱ Epistemology ነው። Epistemology ስለ እውቀት ና ከ


እውቀት ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች የሚያጠና የፍልስፍና ክፍል ነው። በዚህም ምክንያት Epistemology በሌላ ስሙ "Theory
of knowledge" በመባል ይጠራል። Epistemology እውቀት ከዬት መጣ? እውቀት ከምንድን ና እንዴት ነው የሚገኘው?
የዕውቀት ምንጩ ምንድን ነው? ብሎ ይጠይቃል። ለዚህም የራሱን መልስ አስቀምጧል። በ Epistemology መላምት መሰረት
፤ የ እውቀት ምንጮች(sources of knowledge) አምስት ናቸው ወይም አምስት የ እውቀት ማግኛ ዘዴዎች አሉ።
እነርሱም
• Empiricism
• Rationalism
• Intuition
• Revelation
• Authority ናቸው። ስለ አምስቱም ቲቶርያሉ ላይ በሰፊው ከግልፅ ማብራሪያ ና ምሳሌ ቀርቧል ፤ ቲቶርያሉ
ላይ መመልከት ትችላላችሁ። ፈተና ላይ ስለማይቀሩ በደንብ ያዟቸው።

ከ አምስቱ የ ዕውቀት ማግኛ ዘዴዎች አንዱ Empiricism ነው። እንዴ Empircism አስተምህሮ ፤ እውቀት የሚገኘው በ
ስሜት ህዋሳት(sense organs) ነው ይለናል። እንዴት በስሜት ህዋሳት ነገሮችን እንደምናውቅና የዚህ አስተምህሮ ደካማ
ጎን ምን እንደሆነ ቲቶርያሉ ላይ በሰፊው ተምረንዋል። ቲቶርያሉ ላይ መመልከት ትችላላችሁ።

Register @Aplustutoriallbot
JOIN @Aplustutorialofficial

ጥያቄው ግን የሚለው በ Empiricism አስተምህሮ መሰረት ፤ የ እውቀት ምንጩ reason ነው ይላል። ነገር ግን reason
ሳይሆን sense organ ነው የእውቀት ምንጩ አንደ empiricism አስተምህሮ። ስለዚህ መልሱ false ነው። በ
rationalism አስተምህሮ ነው reason የእውቀት ምንጭ ነው የተባለው።

✅ Answer : False

6) According to rationalists, sense can not give us coherent and universally valid
judgement.

6ኛ) ጥያቄው የሚለው: እንደ rationalism አስተምህሮ ፤ የስሜት ህዋሶች(sense) የተደራጀ ፥ የተስተካከለ ና በ
አለምአቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው እውቀትን መስጠት አይችሉም።

☼ Explanation: እንደ Epistemology አስተምህሮ ከ እውቀት ምንጮች(sources of knowledge) መካከል


Empiricism ና Rationalism ተጠቃሽ ናቸው። በ Empircism አስተምህሮ የእውቀት ምንጩ ወይም እውቀት የሚገኘው
በስሜት ህዋሳቶቻችን(sense organs) አማካኝነት ነው ይላል። በ rationalism አስተምህሮ ደግሞ የሰው ልጅ በስሜት
ህዋሳቶቹ የሚያገኘው ዕውቀት አለምአቀፋዊ ና የተረጋገጠ አይደለም( The senses alone can not provide univeral,
valid judgements that are consistent with each other) ይላል። ዝርዝር ማብራሪያዎቹ ከቲቶርያሉ ላይ አሉ
እነሱን መመልከት ትችላላችሁ። ስለዚህ መልሱ true ነው ማለት ነው።

✅ Answer : True.

7) Philosophy is something that can be mastered through school learning and


deals with not specific subject matter, rather issues of universal in nature.

7ኛ) ጥያቄው የሚለው: ፍልስፍና ን ትምህርት ቤት ገብተን በመማር ነው ፈላስፋ መሆን የምንችለው ወይም የፍልስፍና ሊቅ
መሆን የምንችለው ፤ እንዲሁም ደግሞ ፍልስፍና አንድን ጉዳይ(specific matter ብቻ የሚዳስሳ ሳይሆን አለምአቀፋዊ የሆኑ
ጉዳዮችን የሚዳስስ ነው።

☼ Explanation: ትክክል ነው ፍልስፍና ስለ አንድ ጉዳይ ብቻ የሚያወራ አይደለም። እነ chemistry, biology ወዘተ
አንድን ነገር ነጥለው የሚያጠኑ ና የሚዳስሱ ናቸው ፤ ለምሳሌ Chemistry ስለ matter ነው የሚያጠናው ፥ Biology ስለ
life ነው የሚያጠናው። ስለዚህ Chemistry ና Biology specific subject matter አላቸው ማለት ነው እነርሱም
matter ና life ናቸው። ፍልስፍና ግን ይህ ነው የሚባል specific subject matter የለውም። የማይገባበት የማይዳስሰው
የለውም፤ ስለ universe ና በ universe ውስጥ ስላሉ ነገሮች በሙሉ ያጠናል ይመራመራል ይጠይቃል ፤ ፍለጋው ና ጉዞው
ገደብ አልባ ነው። በዚህም ምክንያት philosophy specific subject matter የለውም ፤ univeral nature ነው
ያለው። ነገር ግን የፍልስፍና ሊቅ ወይም ፈላስፋ የሚኮነው ትምህርት ቤት ገብቶ በመማር ነው እንዴ? እነ Aristotle ኮሌጅ
ገብተው ተምረው ነው ዴ የፍልስፍና አባት የሆኑት? እነ ሶቅራጥስ እነ ጆን ሎክ እነ ቶማስ ሆብስ እነ አማኑኤል ካንት ወዘተ
ትምህርት ቤት ገብተው ተምረው ነው እንዴ የፈላስፋ ሊቅ የሆኑት? አይደለም። ፈላስፋ መሆን የሚቻለው ትምህርት ቤት ገብቶ
በመማር አይደለም። ይልቁንም በአለም ና በውስጧ ያሉት ነገሮች ላይ መደነቅ ፥ መገረም ፥ ትኩረት መስጠት ፥ ማሰላሰል ና
መመሰጥ እንዲሁም ያልተገደበ ምክንያታዊ ፍለጋ በማድረግ የሚገኝ የ ዕድሜ ልክ ስራ ነው። ስለዚህ ፈላስፋ መሆን የሚቻለው
ትምህርት ቤት ገብቶ በመማር ነው( philosophy is mastered through school learning) የሚለው ሀሳብ ስህተት
ነው። ስለዚህ መልሱ false ነው።

✅ Answer : False

8) Philosophical wisdom is the wisdom of the expertises or technical skills of


professionals.

8ኛ) ጥያቄው የሚለው: philosophical wisdom ማለት በአንድ ነገር(ስራ) ላይ የተሰማራ ባለሙያ wisdom ነው።

☼ Explanation : ለምሳሌ አንድ የህክምና ባለሙያ ፤ በህክምና ጉዳዮች ላይ ዕውቀት አለው። ስለዚህ ይህ የህክምና
ባለሙያ wisdom of expertise ወይም technical professional skill አለው ማለት ነው። ሌላ ምሳሌ አንድ
ኢኮኖሚስት ፤ በ ኢኮኖሚክሱ ዘርፍ ዕውቀት አለው። ስለዚህ ይህ ኢኮኖሚስት wisdom of expertise ወይም technical

Register @Aplustutoriallbot
JOIN @Aplustutorialofficial

professional skill አለው ማለት ነው። ስለዚህ ዶክተሩ ና ኢኮኖሚስቱ philosophical wisdom አላቸው ማለት ነው?
ዶክተሩ ና ኢኮኖሚስቱ ፈላስፋ ናቸው ማለት ነው? አይደሉም። philosophical wisdom ማለት በአንድ ጉዳይ ወይም ስራ
ላይ ያለን ዕውቀት ማለት አይደለም። የሆነ ነገር ባለሙያ ፥ የሆነ ነገር ሊቅ ስለሆነ philosophical wisdom አለን ማለት
አይደለም። ምክንያቱም Philosophical wisdom ማለት በተለያዩ ነገሮች ላይ ጭፍን አመለካከት ከመያዝ ይልቅ
ነቂሳዊ[ምክንያታዊ] አመለካከትን የማዳበር ባህል(the development of critical habits) ፤ እውነትን ያለማቋረጥ
የመፈለግ ሒደት(the continuous search for the truth) ፤ በአይናችን የምናየው የምንዳስሰው ግልፅ መስሎ
የሚታዬው ገሀዱ አለም ላይ ስላሉ ነገሮች ጥያቄ ማንሳት መመራመር ና በተለያዬ angle መመልከት(the questioning of
the apparent) ማለት ነው። ስለዚህ እነ Aristotle ፥ Socrates ፥ Epicurus ፥ Jeremy Bentham ወዘተ የ ፈላስፋ
ሊቅ የተባሉት ምክንያታዊ አስተሳሰብ ስላላቸው ፥ እውነት ላይ ለመድረስ እድሜ ልካቸውን ስለኳተኑ ፥ በገሀዱ አለም ላይ
ፍልስፍናዊ ጥያቄዎችን ስላዥጎደጎዱ ነው። ስለዚህ philosophical wisdom technical skill or expertise ማለት
አይደለም። ስለዚህ መልሱ false ነው።

✅ Answer : False

ይህ የስኬትዎ አጋር የሆነው A+ Tutorial Class ነው። የ


2016 ፍሬሽማን ሆነው ካልተመዘገቡ ፤ በ
@Aplustutoriallbot በመመዝገብ ትምህርቱ ን
መከታተል ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ ይፋዊ የቴሌግራም
ቻናላችን(@Aplustutorialofficial) ን ይቀላቀሉ።
እሺ አሁን ደግሞ ወደ Part II እናምራ
...

Part II : Choose the best answer from the given alternatives.

9) Which of the following claims that human beings are born with thinking
capability?

A) Empiricism
B) Authority
C) Rationalism
D) Revelation

ጥያቄው የሚለው: የሰው ልጆች የማሰብ ችሎታ በተፈጥሮ የተሰጣቸው ናቸው የሚለው አስተምህሮ የማን ነው?

☼ Explanation: ምርጫዎቹን ስንመለከት አራቱም የ sources of knowledge አይነቶች ናቸው። የማሰብ


ችሎታ(thinking capability) ማለት ምክንያታዊ መሆን መቻል ማለት ነው። ነገሮችን በምክንያት ማድረግ ፥ ነገሮችን
በምክንያታዊነት መዳኘት(rational judgement) መቻል ማለት ነው። ምክንያታዊነት ደግሞ የ Rationalism አስተምህሮ
ነው። ስለዚህ መልሱ C ነው ማለት ነው።

✅ Answer : C

Register @Aplustutoriallbot
JOIN @Aplustutorialofficial

10) Which of the following statement is incorrect?

A) Because of its universality, philosophy is incomprehensible.


B) Questioning is one of the essential attributes of philosophy.
C) Philosophical questions do not have clear cut solution.
D) Criticism is the ultimate objective of Philosophy.

ጥያቄው የሚለው: ከቀረቡት አማራጮች ውስጥ የተሳሳተ ሀሳብ ን የያዘው የትኛው ነው?

☼ Explanation: ምርጫ A ን እንመልከት ፤ ፍልስፍና አለምአቀፋዊ ባህሪይ ከመላበሱ አንፃር ፤ ፍልስፍናን መረዳት
ይከብዳል። የሚል ነው። ፍልስፍና አለምአቀፋዊ(universal) ነው ማለት ፤ ስለ አንዲት ጉዳይ ብቻ የሚያጠና ሳይሆን በቁጥር
ሊገለፁ የማይችሉ እጅግ በጣም በርካታ ጉዳዮችን የሚያጠና የሚዳስስ ነው እንደማለት ነው ፤ ከሰው ልጆች አዕምሮ መረዳት ና
ዕውቀት በላይ(Beyound the limit of human knowledge) ስለ universe የሚያጠና ነው። በዚህም ምክንያት ፍልስፍና
ን እንዲሁ መረዳት የማይቻል(incomprehensible) ነው። ስለዚህ ምርጫ A ትክክል ነው። ምርጫ B እንመልከት ፤
መጠዬቅ(questioning) የፍልስፍና አንዱ አስፈላጊ መገለጫ ባህሪው ነው ፤ ይላል። የ ፍልስፍና ሞሰሶዎች ወይም መሰረቶች
ከሆኑት መካከል መደነቅ(wonder) ና መጠዬቅ(questioning) ናቸው። ፍልስፍና በራሱ ስለ universe ና በ ውስጧ
ስላሉት ነገሮች መጠዬቅ መመራመር መፈላሰፍ ማለት ነው። መጠዬቅ ስንል ትርከምርኪ የመንደሬ ወሬ አይደለም። አርሰናል
ስንት ለስንት አሸነፈ? ሽንኩርት ስንት ገባ? ልብሱን ስንት ብር ገዛሽው? ምሳ በልተሀል? ወዘተ ና የመሳሰሉት የዕለት ተዕለት
ህይወትቻን ውስጥ ያሉት ጥያቄዎች የፍልስፍና ጥያቄወዎች አይደሉም። ይልቁንም ስለ ተፈጥሮ ፥ ስለ ሰው ልጅ ማንነት ፥ ስለ
ውበት ፥ ስለ ዕውቀት ፥ ስለ ስነ-ምግባር ፥ ስለ ፈጣሪ ወዘተ መጠዬቅ መመራመር ነው ፈልስፍናን በርግጥም ፍልስፍና ያስባለው።
ፈጣሪ አለ? ካለስ ማረጋገጫው ምንድን ነው? ውበት ውስጣዊ ነው ወይስ ውጫዊ? አንድ ሰው ባንክ ዘርፎ ብሩን ለድሆች
ቢሰጥ ይህ ሰው ትክክል ነው ወይስ ስህተት ነው? የዕውቀት መለኪያው ምንድን ነው? ቋንቋ ምንድን ነው? ሰዎች እንዴት
ተግባቡ? ወዘተ ሐጠዬቅ መቻል ነው ፍልስፍና። ስለዚህ መጠዬቅ የፍልስፍና አንዱ መገለጫ ነው። ምርጫ B ትክክል ነው።
ምርጫ C ን እንመልከት ፤ የፍልስፍና ጥያቄዎች ትክክለኛ የተረጋገጠ መልስ የላቸውም። ይላል። ፈጣሪ አለ? ለሚለው ጥያቄ
የተረጋገጠ ቀጥተኛ ና የተጨበጠ መልስ ማግኘት አይቻልም። ከሀይማኖት አንፃር ማለቴ አይደለም። ውበት ውስጣዊ ወይስ ውጫዊ?
ለሚለው ጥያቄ ሁሉንም የሚያስማማ ትክክለኛ መልስ የለውም። ስለዚህ ፍልስፍና ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ግልፅ የማያሻማ
ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል መልስ ማግኘት ብርቅ ነው ፤ ስለዚህ ምርጫ C ትክክል ነው። ምርጫ D ግን ስህተት ነው።
ምክንያቱም መተቸት መንቀፍ(criticism) የፍልስፍና ዋና አላማ አይደልም።

✅ Answer : D

11) Which of the following questions is not primarily the question of Axiology?

A) What is the nature of ultimate reality?


B) What is the right thing to do?
C) What is beauty?
D) What political system is best?

ጥያቄው የሚለው: ከሚከተሉት የፍልስፍና ጥያቄዎች መካከል Axiology በሚያነሳቸው የፍልስፍና ጥያቄዎች ውስጥ
የማይካተተው የትኛው ነው? የሚል ነው።

☼ Explanation: Axiology ማለት ስለ እሴት(value) የሚያጠና ነው ብለናል። ስለዚህ ከ value ጋ የሚገናኙ


ጥያቄዎችን ነው የሚያነሳው ማለት ነው። ምርጫ B ን እንመልከት ፡ ትክክለኛ ድርጊት የሚባለው የትኛው? ይህ ጥያቄ የ
normative Ethics ጥያቄ ነው ፤ Normative Ethics ደግሞ የ Axiology አይነት ነው ስለዚህ ምርጫ B ላይ የቀረበው
ጥያቄ በ Axiology ውስጥ የሚካተት የፍልስፍና ጥያቄ ነው። ምርጫ C ን እንመልከት ፡ ውበት ምንድን ነው? ስለ ውበት
የሚያጠናው Aesthetics ነው። ስለዚህ ይህ የ Aesthetics ጥያቄ ነው። Aesthetics ደግሞ የ Axiology አይነት ነው።
ስለዚህ ምርጫ C ላይ የቀረበው ጥያቄ በ Axiology ውስጥ የሚካተት የፍልስፍና ጥያቄ ነው። ምርጫ D እንመልከት ፡ የትኛው
የፖለቲካ ስርአት ነው ተስማሚ? ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የሚያጠናው social/political philosophy ነው።
social/political philosophy ደግሞ የ Axiology አይነት ነው። ስለዚህ ምርጫ D ላይ የቀረበው ጥያቄ በ Axiology
ውስጥ የሚካተት የፍልስፍና ጥያቄ ነው። ስለዚህ Ethics, Aesthetics ና social/political philosophy የ axiology
አይነት ናቸው።

Register @Aplustutoriallbot
JOIN @Aplustutorialofficial

ምርጫ A ን እንመልከት ፡ መገኘት መፈጠር መኖር(reality) ማለት ምን ማለት ነው? ስለ reality(existence)


የሚያጠናው የፍልስፍና ክፍል ደግሞ Metaphysics ነው። ስለዚህ ምርጫ A ላይ የቀረበው የፍልስፍና ጥያቄ ፥ በ axiology
ውስጥ ሳይሆን የሚካተተው በ metaphysics ነው። ስለዚህ መልሱ ምርጫ A ነው።

✅ Answer : A

12) One of the following is not the concern of Metaphysics. Which one?

A) The source of human knowledge.


B) Origin, nature and development of the universe.
C) The concept of God.
D) The study of human beings.
E) Nature and meaning of existence.

ጥያቄው የሚለው: ከሚከተሉት ውስጥ የ metaphysics ጥናት ያልሆነው የትኛው ነው?

☼ Explanation: Metaphysics ስለ መገኘት መፈጠር(reality/existence) የሚያጠና ሲሆን በ አራት ይከፈላል


እነርሱም Anthropology, Cosmology, Ontology ና Theology ናቸው። Anthropology ስለ ሰው ልጆች አመጣጥ
፤ ባህል ፤ አካላዊ ና አዕምሯዊ መስተጋብር በአጠቃላይ ሰለ ሰው ልጆች ነው የሚየጠናው(the study of human being)።
ስለዚህ ምርጫ D የ metaphysics አንዱ ጥናት ነው ማለት ነው። Cosmology የሚያጠናው ስለ universe አመጣጥ ፥
አፈጣጠር ና እድገት ነው የሚያጠናው(origin, nature and development of universe)። ስለዚህ ምርጫ B የ
metaphysics አንዱ ጥናት ነው ማለት ነው። Ontology የሚያጠናው ስለ መገኘት መፈጠር ነው(nature and meaning
of existence)። ስለዚህ ምርጫ E የ metaphysics አንዱ ጥናት ነው ማለት ነው። Theology የሚያጠናው ደግሞ ስለ
ፈጣሪ ነው ፤ ፈጣሪ አለ ብሎ የሚያስተምር ነው(The concept of God)። ስለዚህ ምርጫ C የ metaphysics አንዱ ጥናት
ነው ማለት ነው። ማን ቀረ? ምርጫ A ቀረ። The source of human knowledge(ስለ ዕውቀት ምንጮች)
የሚያጠናው Epistemology ነው እንጂ metaphysics አይደለም። ስለዚህ ምርጫ A ነው መልስ የሚሆነው።

✅ Answer : A

13) Of the following, one branch of epistemology claims that true knowledge can
only be achieved through experience:

A) Ontology
B) Empiricism
C) Revelation
D) Rationalism

ጥያቄው የሚለው: ትክክለኛ እውቀት የሚገኘው በ ልምድ(experience) ብቻ ነው የሚል አስተምህሮ የሚያንፀባርቀው


የትኛው የ Epistemology አይነት ነው?

☼ Explanation: Ontology የ Epistemology አይነት ስላልሆነ ምርጫ A ከወዲሁ ጥለንዋል። በ Empiricism


አስተምህሮ መሰረት ፤ ዕውቀት የሚገኘው በ ስሜት ህዋሶቻችን አማካኝነት ነው የሚል ነው። ስለዚህ እውቀት እየተሻሻለ
እየተገነባ የሚሔደው የሰው ልጆ በነገሮች ላይ በቂ ልምድ(experience) እያካበቱ ሲሔዱ ነው ፤ ማለትም የስሜት
ህዋሳቶቻቸው ነገሮችን የመረዳት አቅማቸው እያደገና እየሰፋ ሲመጣ ነው። ስለዚህ በ Empiricism አስተምህሮ መሰረት ፥
ሰዎች በስሜት ህዋሶቻው አማካኝነት ነገሮች ላይ የሚያካብቱት ልምድ(experience) ፥ የ ዕውቀት ምንጭ ነው። ስለዚህ
እንደ Empircism አስተምህሮ ልምድ(experience) ዕውቀት ማግኛ ዘዴ ነው። ስለዚህ መልሱ A ነው።

✅ Answer : A

Register @Aplustutoriallbot
JOIN @Aplustutorialofficial

14) Which of the following best characterizes the basic nature of philosophy?

A) Philosophy is a tree like discipline that comprises of basic branches that deal
with the totality of the universe that deal with fundamental questions and
multi-layered approach.
B) Philosophy has no practical importance for the poor people of "third-world"
nations.
C) Philosophy is a discipline assisted by laboratory experiments to understand
material problems.
D) Philosophy deals with superficial problems that we encounter in our daily
societial and conventional lives.

ጥያቄው የሚለው: ከቀረቡት አማራጮች ውስጥ የ ፍልስፍናን መሰረታዊ ባህሪ በጥሩ ሁኔታ የሚገልፀው አማራጭ የትኛው
ነው?

☼ Explanation: ምርጫ A ን እንመልከት ፥ ዛፍ በርካታ ቅርንጫፎች አሉት። ፍልስፍና ም ልክ እንደ ዛፍ(tree like)
የሆነ የሙያ ዘርፍ ነው ፤ በርካታ ቅርንጫፎች(branches) አሉት ፥ እነዚህ ቅርንጫፎች ደግሞ ስለ universe ምንነት
የሚያጠኑ ፤ መሰረታዊ ጥያቄዎችን የሚጠይቁ ና ለምርምራቸው በርካታ ዘዴዎችን የሚጠቀሙ ናቸው ፤ ይላል። ትክክል ነው
ፍልስፍና ልክ እንደ ዛፍ በርካታ ቅርንጫፎች አሉት። እነርሱም Metaphysics, Epistemology, Axiology ና Logic
ናቸው። Metaphysics በ 4 ይከፈልላል ፤ Epistemology በ 5 ይከፈላል ፤ Axiology በ 3 ይከፈላል። ስለዚህ
ፍልስፍና በርካታ ቅርንጫፎች አሉት ፤ የ ፍልስፍና ሁሉም ቅርንጫፎች የሚያጠኑት ስለ universe ነው ፤ universe ውስጥ
ባሉ ነገሮች ላይ መሰረታዊ ጥያቄዎችን በማንሳት ይመራመራሉ ፤ ለፍልስፍናቸውም የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። ስለዚህ
ምርጫ A ፍልስፍናን በጥሩ ሁኔታ ገልፆታል።
ምርጫ B እንመልከት ፤ ሶስተኛው አለም እየተባሉ ለሚጠሩት ድሀ ሀገራት ፍልስፍና በተግባር የሚሰጠው ጥቅም የለም ፤ ይላል።
ፍልስፍና ለ ሀብታም ሀገር ና ለ ድሀ ሀገር ተብሎ አይከፈልም። ሁሉም የሰው ልጆች በ universe ውስጥ እስካሉ ድረስ ፥
የመደነቅ የማሰብ የመመሰጥ ና የመጠዬቅ ዝንባሌ እስካላቸው ድረስ ሁሉም የሰው ልጆች መፈላሰፍና ከፍልስፍና ጥቅምን
ማግኘት ይችላሉ። ስለዚህ ምርጫ B ፍልስፍናን መግለፅ አይችልም። ምርጫ C እንመልከት ፤ ፍልስፍና ችግሮችን ለመፍታት
ነገሮችን ለመረዳት በ Laboratory experiment የሚደገፍ የሙያ ዘርፍ ነው ፤ ይላል። በአጭሩ ፍልስፍና laboratory
experiment አይጠቀምም። ምርጫ D እንመልከት ፥ ፍልስፍና በዕለት ተዕለት ማህበራዊ ና መደበኛ የተለመደ(conventional)
ህይወታችን የሚያጋጥሙንን ጥቃቅን(superficial) የሆኑ ችግሮችን የሚያጠና ነው ፤ ይላል። በመሰረቱ ፍልስፍና
superficial(ጥቃቅን) የሆኑ የዕለት ተዕለት ጉዳዮች ላይ ግድ አይሰጠውም። በርበሬ ስንት ግባ? ባይደን ና ፑቲን ተጣሉ ፤
መኪና 2ሚሊዮን ብር ገባ ወዘተ የሚሉ ጉዳዮች ላይ ድርሽ አይልም። ይልቁንም ከ ሰው ልጆች የማሰብ ና የመረዳት አቅም
በላይ የሆኑ ፤ ትክክለኛነታቸው በሳይንሳዊ መንገድ ያልተረጋገጡ አወዛጋቢ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚሰጠው።
ስለዚህ ምርጫ D ፍልስፍናን መግለፅ አይችልም። ስለዚህ ምርጫ A ፍልስፍናን በጥሩ ሁኔታ ይገልፀዋል።

✅ Answer : A.

15) Philosophy as a "love of wisdom" can be best explained as ________

A) an endless quest for knowledge.


B) unlimited material desire.
C) it state of being very sensual to the people around us.
D) It is the search for particular truth that we love it.

ጥያቄው የሚለው: ፍልስፍና "love of wisdom[ጥበብን መፈለግ]" ሲባል ፤ ምን ማለት ነው? የሚል ነው።

☼ Explanation: ምርጫ A እንመልከት ፥ እውቀትን ና እውነትን ለማግኘት የሚደረግ ረዥም የማያቋርጥ ፍለጋ
ነው(an endless quest for knowledge)። ምርጫ A ትክክል ነው ፤ love of wisdom ማለት ጥበብን ና እውቀትን
መፈለግ መሻት ማለት ነው። በሌላ አባባል እውቀትን መጠማት እውቀት ላይ ለመድረስ መጓጓት መናኘት ማለት ነው love of
wisdom ማለት። ስለዚህ ስለዚህ እውቀትን ለማግኘት የማያቋርጥ የዕድሜ ልክ ጉዞ ና ፍለጋ ማድረግ love of wisdom ነው።
እውቀት(wisdom)ን ስናፈቅረው(love) ስንፈልገው ነው አይደል ሙሉ ህይወታችንን ሰጥተን እሱን ፍለጋ የምንከተለው።

Register @Aplustutoriallbot
JOIN @Aplustutorialofficial

አባታችን አብርሀም ፈጣሪው(እውነት) ን ፍለጋ ከቤተሰቦቹ ተጥሎ ወደ ማያውቀው ሀገር ወደ ከነአን በእምነት ተሰዷል።
ለምን? love of wisdom ስላለው። እነ ሶቅራጥስ እነ ጆን ሎክ ስለ universe ለማወቅ ሙሉ ህይወታቸውን ሰውተዋል።
love of wisdom ስላላቸው። ምርጫ B ን እንመልከት ፤ love of wisdom ማለት ያልተገደበ የገንዘብ መሻት(unlimited
material desire) ነው ይላል ምርጫ B። ሲጀመር ፍልስፍና ከገንዘብ ና ከአለማዊ ቁሶች ጋ ግንኙነት የለውም። ስህተት
ነው ምርጫ B። ምርጫ C ደግሞ አለማዊ ስጋዊ(sensual) መሆን ማለት ነው ይላል። ስህተት ነው ፤ ፍልስፍና የስጋ ፍትወት ና
ምኞት የለውም። ምርጫ D ደግሞ ፥ አንድ ማውቅ የምንፈልገውን ነገር ለማወቅ የምናደርገው ፍለጋ ነው ይላል። ፍልስፍና
particular(specific) አይደለም ፤ ማለትም ስለ አንድ ነገር ብቻ ወይም አንድን ነገር ለይቶ የሚያጠና አይደለም። ስለ
universe ነው የሚያጠናው ስለዚህ ምርጫ D ስህተት ነው። መልሱ A ነው።

✅ Answer : A.

16) Which of the following axiological efforts attempts to apply ethical


standards to specific moral problem?

A) Applied Ethics.
B) Meta Ethics.
C) Normative Ethics.
D) Moral Emotivism.

ጥያቄው የሚለው: Moral problem አንዱ ወገን መደረግ አለበት ብሎ የሚከራከርለት ሌላኛው ወገን ደግሞ አይ መደረግ
የለበትም ብሎ የሚከራከርለት አወዛጋ አከራካሪ(controversial) ጉዳይ ማለት ነው ፤ ለምሳሌ እንስሳቶች ለምግብነት
መታረድ አለባቸው ወይስ የሚለባቸው የሚለው ሁለት ወገኖችን የሚያከራክር ነው ፥ ሌላ ምሳሌ ማስወረድ ተገቢ ነው ወይስ
አይደለም የሚለው ሁለት ወገኖችን የሚያከራክር ነው ፥ ለድሆች ብር መስጠት ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው አከራካሪ
ነው ፤ ስለዚህ Animal right, Abortion, Giving to the poor, sex before marriage, Lesbian/gay sex,
The death penality, Adultery(ዝሙት) , euthanasia(ራስን ማጥፋት) , capital punishement(የሞት
ፍርድ) ወዘተ moral problem ናቸው። ጥያቄው የሚለው በ አንድ በሆነ moral problem ላይ የስነ-ምግባር
መሮሆዎች(ethical standard) ን ለመተግበር የሚሞክረው የ Axiology አይነት ማነው? የሚል ነው።

☼ Explanation: አወዛጋቢ አካራካሪ በሆኑ moral problems ላይ ጥናት የሚያደርገው ና ከስነ-ምግባር መርሆዎች
አንፃር ስለ moral problems ትክለለኛነት ወይም ስህተትነት የሚተነትነው የ Ethics አይነት Applied Ethics ነው። ስለዚህ
መልሱ A ነው ማለት ነው።

✅ Answer : A.

17) Wisdom for philosophers is not:

A) The development of critical habit.


B) Technical skills of professionals.
C) The continuous search for truth.
D) The questioning of the apparent.
E) All except C.

ጥያቄው የሚለው: ለፈላስፋፎች wisdom የሚለውን ትርጉም በትክክል የማይገልፀው የትኛው ነው? የሚል ነው።

☼ Explanation: ምርጫ A ን እንመልከት ፥ ምክንያታዊ አስተሳሰብን የማዳበር ባህል(the development of


critical habits) ነው ይላል። ትክክል ነው ፥ ከ love of wisdom አንፃፍ ፍልስፍና በጉዳዮች ላይ ምክንያታዊ መሆን ማለት
ነው። ምርጫ B ን እንመልከት ፥ በሆነ ሙያ በሆነ ዘርፍ ላይ ያለ ዕውቀት(technical skills of professionals) ነው
ይላል። ምርጫ B ስህተት ነው። ለምሳሌ በህክምና ሙያ ወይም ዘርፍ ላይ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ስለ ህክምና
ዕውቀት(technical skill/wisdom) አላቸው ፤ ነገር ግን የህክምና ባለሙያዎች ፈላስፋ ናቸው እንዴ? አይደሉም።
ስለዚህ የፍልስፍና wisdom(እውቀት) ፤ በሆነ ሙያ ዘርፍ ውስጥ ካለ ዕውቀት(wisdom/technical skill) ጋ ተመሳሳይ
አይደለም። ምርጫ C ን እንመልከት ፤ እውነትን ያለማቋረጥ መፈለግ ነው ይላል። ምርጫ C ትክክል ነው። ከ love of
wisdom አንፃር ፥ ፍልስፍና እውነትን ለማግኘት ያለማቋረጥ የሚደረግ ፍለጋ ነው። ምርጫ D ም ትክክል ነው ምክንያቱም ከ

Register @Aplustutoriallbot
JOIN @Aplustutorialofficial

love of wisdom አንፃር ፥ ፍልስፍና ገሀዱ አለም ላይ ጥያቄ ማንሳት ነው። ስለዚህ ከ love of wisdom አንፃፍ
ፍልስፍና(philosophical wisdom) ማለት
• The development of critical habits.
• The continuous search for the truth.
• The questioning of the apparent ማለት ነው። ቲቶርያሉ ላይ ተምረንዋል መመልከት ትችላላችሁ።

18) One is not a basic question in philosophy, which one?

A) Where did the universe come from?


B) Are animals moral agents or moral subjects?
C) What time is it?
D) What is an argument?

ጥያቄው የሚለው: ከቀረቡት አማራጮች መካከል ፍልስፍናዊ ጥያቄ ያልሆነው የትኛው ነው? የሚል ነው።

☼ Explanation: philosophical question(የፍልስፍና ጥያቄ) ማለት ፤ በሳይንስ ያልተረጋገጡ ፥ 100% ትክክል


ናቸው ተብሎ ያልተደመደሙ አስተማማኝ ማረጋገጫ መልስ ያልተገኘላቸው ፥ ከሰው ልጆች እውቀት ና መረዳት በላይ የሆኑ
የሰው ልጆች ለመመለስ የሚቸገርባቸው አወዛጋቢ ጥያቄዎች ናቸው። ምርጫ A እንመልከት ፤ universe ከዬት ነው የመጣው?
ለዚህ ጥያቄ በሳይንስ የተረጋገጠ መልስ አለ? የለም። ስለዚህ philosophical question ነው ፤ እንደውም የ metaphysics
question ነው። ስለዚህ ምርጫ A ትክክል ነው። እንስሳቶች መብት አላቸው(moral agents) ወይስ የሰው ልጆች ን
ፍላጎት ለማሳካት የተፈጠሩ በሰው ልጆች ቁጥጥር ስር ያሉ ናቸው(moral subjects) ? ለዚህ ጥያቄ ትክክለኛ የተረጋገጠ
መልስ ማቅረብ ይቻላል? አይቻልም። አወዛጋቢ አከራካሪ ጥያቄ ነው ፤ እንደውም ይህ ጥያቄ የ Applied Ethics(axiology)
ጥያቄ ነው። ስለዚህ ምርጫ B ትክክል ነው። ምርጫ C እንመልከት ፤ ስንት ሰአት ነው? ለዚህ ጥያቄ ትክክለኛ የተረጋገጠ መልስ
መስጠት ይቻላል? አዎ ይቻላል። 5:10 ነው ፤ 12 ሰአት ነው ፤ 9 ሰአት ነው ወዘተ ብሎ መስጠት ይቻላል። ስለዚህ መልሱን
በትክክል ማወቅ ስለሚቻል ይህ ጥያቄ philosophical question አይደለም፤ ምንም የሚያፈላስፍ ነገር የለወም። ስለዚህ
ምርጫ C ነው መልሱ።

✅ Answer : C

19) "Is basic reality found in matter or in spirit?" This question can be asked
under:

A) Theological
B) Ontological
C) Anthropological
D) Cosmological

ጥያቄው የሚለው: "ገሀዱ አለም(reality) የተገኘው ከቁስ አካል ነው ወይስ ከ መንፈሳዊ ሀይል?" የሚለውን ጥያቄ
የሚጠይቀው የትኛው አማራጭ ነው?

☼ Explanation: አራቱ ምርጫዎች የ metaphysics አይነት ናቸው። Theology የሚያጠናው ስለ ፈጣሪ ህልውና ነው
፤ ፈጣሪ አለ ብሎ የሚያስተምር ነው። ስለ ፈጣሪ ነው እንጂ ስለ reality አያጠናም። ስለዚህ ምርጫ A አይሆንም። Ontology
ደግሞ የሚያጠናው ስለ ገሀዱ አለም አፈጣጠር ና ባህሪ(reality/existence) ነው። ከ ontology ጥናቶቹ አንዱ ፤ ገሀዱ
አለም የተፈጠረው በ መንፈሳዊ ሀይል ነው ወይስ በቁስ አካላት ወይስ በ physical energy? ነው የሚል ነው። ስለዚህ መልሱ
B ነው። ቲቶርያሉ ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ስላለ መመልከት ትችላላችሁ ፤ ስለ 4 ቱ የ metaphysics አይነቶች
ማለት ነው።

✅ Answer : B

Register @Aplustutoriallbot
JOIN @Aplustutorialofficial

20) A central aim of philosophy is:

A) to learn how to win arguments and influence people.


B) to prove that others are ignorant and foolish.
C) to free the mind of any and all assumptions.
D) to acquire self-understanding.
E) C and D.

ጥያቄው የሚለው: የፍልስፍና አላማ የቱ ነው? የሚል ነው።

☼ Explanation: ፍልስፍና መማራችን ጥቅሙ ምን ይሆን? በ ገሀዱ አለም ላይ መፈላሰፋችን ጥቅሙ ምን ይሆን?
ምርጫ A እንመልከት ፤ በክርክር ሰዎች እንዴት ማሸነፍ እንዳለብን ለመማር ነው ዋና አላማዉ ይላል። ክርክር ማሸነፍ
የፍልስፍና ዋና አላማ አይደለም ፤ ስለዚህ A ስህተት ነው። ምርጫ B እንመልከት ፤ ሌሎች ሰዎች መሀይም ና አላዋቂ እንደሆኑ
ለማረጋገጥ ነው ዋና አላማው ይላል። ስህተት ነው የሌሎችን አለማወቅ ለማጋለጥ አይደለም የፍልስፍና አላማ። ምርጫ C
እንመልከት ፤ በአዕምሯችን ውስጥ ይሆናሉ ብለን ያሰብናቸውን የገመትናቸውን ነገሮች ለማፅዳት(free) ነው አላማው
ይላል። ስህተት ነው፤ ሲጀመር ፍልስፍና የሚጀምረው ከ assumption ነው። እነዚህ assumption ኖች ደግሞ ትክክለኛ ና
የተረጋገጠ መልስ ስለሌላቸው free መሆን አይችሉም። ምርጫ D ን እንመልከት ፤ ራስን ለማወቅ ራስን ለመረዳት ነው ዋና
አላማው ይላል። ይሔ ትክክል ነው።

✅ Answer : D

21) One of the following statement is correct about philosophy፡

A) It is not interested in issues that other disciplines have adressed in any form.
B) Practically speaking, philosophy is not helpful in adressing societal problem
at all.
C) It doesn't have any defined scope.
D) It is an indescribable discipline.
E) none

ጥያቄው የሚለው: ከሚከተሉት አማራጮች ውስጥ ስለ ፍልስፍና ትክክል የሆነው አማራጭ የትኛው ነው?

☼ Explanation: ምርጫ A እንመልከት ፥ ሌሎች የሙያ ዘርፎች ያጠኗቸው ጉዳዮች ላይ ፍልስፍና የመሳተፍ ፍላጎት
የለውም ይላል። ስህተት ነው ሲጀመር ፍልስፍና ሁሉንም(universal) ጉዳይ ከመዳሰስ ከመጠዬቅ ወደሗላ አይልም።
ምርጫ B እንመልከት ፤ ከተግባር አንፃር ፍልስፍና ማህበረሰባዊ ችግሮችን ከመፍታት አንፃር ምንም ጥቅም የለውም ይላል።
ስህተት ነው ፤ የሰውን ልጅ ችግር የሚፈቱ አዳዲስ ግኝቶች የሚገኙት በጉዳዮች በችግሮች ላይ በመጠዬቅ በመፈላሰፍ ነው።
ምርጫ C ን እንመልከት ፤ ፍልስፍና ውስን ያለ የሚገለፅ scope የለውም ይላል። እውነት ነው ፤ scope ማለት ገደብን ስፋትን
ድንበርን እስከዬት ድረስ ነው የሚለውን የሚገልፅ ነው። ለምሳሌ የ chemistry scope matter ነው። የ biology scope
life ነው። የ ፍልስፍና ይህ ነው ተብሎ የሚነገር ገደብ ድንበር(scope) አለው? የለውም።ስለሆነ ነገር ያጠናል ተብሎ
አይገለፅም ስለ ሁሉም ነገር ይዳስሳል፤ በዚህም ምክንያት scope የለውም ወይም እስከዬት ደረስ እንደሚያጠና በግልፅ
አይታወቅም። ስለዚህ ምርጫ C ትክክል ነው። ምርጫ C እንመልከት ፤ ፍልስፍናን መግለፅ የማይቻል(indescribable)
የሙያ ዘርፍ ነው ይላል። chemistry ን ወይም biology ን መግለፅ በምንችልበት መንገድ ፤ ፍልስፍናን በርግጥ መግለፅ
ይከብዳል። ነገር ግን ሳይንስ እስከሆነ ድረስ ፍልስፍናን describe ማድረግ ይቻላል። ስለ universe የሚያጠና ነው ፤ ውስጣዊ
አስተሳሰባችን ና እምነታችንን የምናፀባርቅበት ነው ወዘተ እያልን ፍልስፍናን መግለፅ ይቻላል። Basic features of
philosophy በሚል ርዕስ ቲቶርያሉ ላይ ተምረናል። እዛ ላይ ሒዳችሁ ፍልስፍና የተገለፀበትን መንገድ መመልከት ትችላላችሁ።
ስለዚህ ፍልስፍና describable ነው።

✅ Answer : C

Register @Aplustutoriallbot
JOIN @Aplustutorialofficial

22) Which of the following is FALSE regarding philosophy?

A) Having philosophy and doing philosophy are interdependent.


B) Systematic reflection about the whole reality.
C) Doing philosophy is a formal sense of philosophy, where as having philosophy
is not sufficient for doing philosophy.
D) Systematic reflection about individual matters.
E) Works beyound the limit of knowledge.

ቀላል ነው ማብራራት አያስፈልገውም።

✅ Answer : D

23) The cosmological aspect of metaphysics deals with one of the following
except:

A) The relation between mind and body.


B) Free will and determinism.
C) The meaning of life.
D) Immortality of the soul.
E) All

ጥያቄው የሚለው: ከቀረቡት አማራጮች ውስጥ Cosmology የተባለው የ metaphysics አይነት የማያጠናው የትኛውን
ነው?

☼ Explanation: ከmetaphysics አይነቶች አንዱ cosmology ነው። cosmological aspect(cosmology)


የሚያጠናው ፤ ስለ universe መነሻነት(origin) ፥ አፈጣጠር(nature) ና ዕድገት(development) የሚያጠና
ነው።universe እንዴት ተፈጠረ? ከተፈጠረ በሗላስ እንዴት አደገ? በአጋጣሚ ይሆን የተፈጠረው ወይስ ታቅዶበት? ወዘተ
የሚሉትን ያጠናል። ምርጫ A ን እንመልክት ፤ አዕምሮ ና አካል ያላቸውን ዝምድና የሚየጠናው Anthropological aspect
ነው። ምርጫ B ን እንመልከት ፤ ስለ ሰዎች ነፃ ፍቃድ(free will) ና ራስን በራስ የማስተዳደር መብት(determinism)
የሚያጠናው Anthropological aspect ነው። ምርጫ C እንመልከት ፤ ስለ ህይወት ትርጉም የሚያጠናው Anthropology
ነው። ምርጫ D ፤ ስለ ነፍስ(soul) ህያውነት የሚያጠናው Anthropology ነው። ስለዚህ አራቱንም አማራጮች
Cosmology አያጠናም። ስለዚህ መልሱ E ነው።

✅ Answer : E

24) Which of the following is not an example of philosophical question?

A) Do numbers exist independently of our thoughts about them?


B) Are minds distinct from our bodies?
C) How many planets are there in the Milky way Galaxy?
D) Does every event have a cause?
E) All

ጥያቄው የሚለው ከሚከተሉት ውስጥ የፍልስፍና ጥያቄ ያልሆነው የትኛው ነው?

☼ Explanation ፡ philosophical question(የፍልስፍና ጥያቄ) ማለት ፤ በሳይንስ ያልተረጋገጡ ፥ 100%


ትክክል ናቸው ተብሎ ያልተደመደሙ አስተማማኝ ማረጋገጫ መልስ ያልተገኘላቸው ፥ ከሰው ልጆች እውቀት ና መረዳት በላይ
የሆኑ የሰው ልጆች ለመመለስ የሚቸገርባቸው አወዛጋቢ ጥያቄዎች ናቸው። ምርጫ A እንመልከት ፤ ከሰዎች አስተሳሰብ ውጭ

1
Register @Aplustutoriallbot
JOIN @Aplustutorialofficial

ቁጥሮች ራሳቸውን ችለው ይገኙ ወይም exist ያደርጉ ይሆን? ሰዎች አስበው አውጥተው አውጥርደው '4' ቁጥርን
ባይሰይሙት ፥ 4 ቁጥር ብቻውን exist ያደርግ ነበር? ለዚህ ጥያቄ የተረጋገጠ መልስ አለ? የለም ፤ ቁጥሮች ከሰው ልጆች
በፊት ይኑሩ ወይም አይኑሩ የሚታወቅ ነገር የለም። ስለዚህ philosophical question ነው ፤ እንደውም ስለ existence
ስለሆነ የሚያወራው የ metaphysics question ነው። ስለዚህ ምርጫ A ትክክል ነው። አዕምሮ ከ አካል ይለያል ፥ ከአካል
ተለይቶ ስራውን መስራት ይችል ይሆን? ለዚህ ጥያቄ ትክክለኛ የተረጋገጠ መልስ ማቅረብ ይቻላል? አይቻልም ፤ እንደውም ይህ
ጥያቄ የ Anthropology(metaphysics) ጥያቄ ነው። ስለዚህ ምርጫ B ትክክል ነው። ምርጫ C እንመልከት ፤ ስንት
ፕላኔቶች አሉ? ለዚህ ጥያቄ ትክክለኛ የተረጋገጠ መልስ መስጠት ይቻላል? አዎ ይቻላል። 9 ፕላኔቶች አሉ ብሎ መልስ መስጠት
ይቻላል። በሳይንስ የተረጋገጠ ነው ፥ ስለዚህ መልሱን በትክክል ማወቅ ስለሚቻል ይህ ጥያቄ philosophical question
አይደለም፤ ምንም የሚያፈላስፍ ነገር የለወም። ስለዚህ ምርጫ C ነው መልሱ።

✅ Answer : C

25) Identify the danger of intuition:

A) It is a safest method of obtaining knowledge.


B) It transcends the limitation of human experience.
C) It is an automatic personal knowledge.
D) It goes astray very easily.

ጥያቄው የሚለው: የ intuition ንን ደካማ ጎን ለይ ነው የሚለው።

☼ Explanation: የ intuition ደካማ ጎን ፤ በ intuition ወይም ድንገት አዕምሯችን ላይ ብልጭ በሚሉ ሀሳቦች
የሚገኝ ዕውቀት ትክክለኛነቱ የተጋገጠ አይደለም ፤ የማፈንገጥ የመውጣት ባህሪ አለው(it goes astray)። ስለዚህ በ
ድንገት አዕምሯችን ውስጥ ብልጭ የሚሉ ሀሳቦች ና ግኝቶች ሳይንሳዊ ሒደትን በመከተል experiment በመስራት
ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ለዚህ እንደ ምሳሌ ቲቶርያሉ ላይ የ Archimedes principle ን አይተናል። በዚህ ጉዳይ
ላይ ሰፊ ማብራሪያ ከፈለጋችሁ ቲቶርያሉ ላይ በቂ ማብራሪያ ታገኛላችሁ።

✅ Answer : D

ይህ የስኬትዎ አጋር የሆነው A+ Tutorial Class ነው። የ


Logic chapter 1 ጥያቄዎችን ከነ ማብራሪያቸው ያዘጋጀው
ከ A+ Tutorial መምህራኖች አንዱ የሆነው Daniel
ነው። በ 0949897546 በመደወል ወይም በቴሌግራም በ
@Aplustutorialowner እንዲሁም በ @NaolGR
ማንኛውንም አስተያዬት ና ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ።
•••

2
Register @Aplustutoriallbot
JOIN @Aplustutorialofficial

Part III : Match the items under column B with those under column A.

Column A Column B
26. Anthropology A) Deals with the value and worth of life.
27. Axiology B) Examines existence in General.
28. Cosmology C) Studies the origins and nature of knowledge.
29. Epistemology D) Claims reason as the source of knowledge.
30. Ontology E) Studies the universe in general.
31. Empiricism F) Deals with origins and development of human
beings.
32. Intuition G) Sense experience is the source of knowledge.
H) Direct or immediate apprehension.
I) The study of nature and purpose of God.

26ኛ) Anthropology የ metaphysics አይነት ሲሆን ፤ የሚያጠናው ስለ ሰው ልጅ አፈጣጠር(origin) ና ዝግመተ


ለውጥ(development) የሚያጠና ነው።
✅ Answer F

27ኛ) Axiology ከ core fields of philosophy አንዱ ሲሆን ፤ ስለ value(እሴት) የሚያጠና ነው።
✅ Answer A

28ኛ) Cosmology የ metaphysics አይነት ሲሆን ፤ ስለ universe አመጣጥ(origin) ፥ አፈጣጠር(nature) ና


አስተዳደግ(development) የሚያጠና ነው።
✅ Answer E

29ኛ) Epistemology ከ core fields of philosophy አንዱ ሲሆን ፤ ስለ እውቀት የሚያጠና ነው።
✅ Answer C

30ኛ) Ontology የ metaphysics አይነት ሲሆን ፤ ስለ ገሀዱ አለም ና ሰለ መገኘት መፈጠር(reality/existence)


የሚያጠና ነው።
✅ Answer B

31ኛ) Empiricism የ Epistemology አይነት ሲሆን ፤ እውቀት የሚገኘው ከ ስሜት ህዋሳቶች(sense) ነው የሚል
አስተምህሮ አለው።
✅ Answer G

32ኛ) intuition የ Epistemology አይነት ሲሆን ፤ በድንገት አዕምሯችን ላይ ብልጭ የሚሉ ሀሳቦች የዕውቀት ምንጭ ናቸው
የሚል አስተምህሮ አለው።
✅ Answer H

© A+ Tutorial Class

3
Register @Aplustutoriallbot

You might also like