ኒው ጊኒ በኦሺያኒያ የተገኘ ታላቅ ደሴት ነው። አሁን በኢንዶኔዥያና በፓፑዋ ኒው ጊኒ ይካፈላል።
ደሴቱ የሸንኮራ ኣገዳ እንዲሁም የሙዝ መነሻ እንደ ሆነ ይታመናል። ከዚህም በላይ በአትክልትም ሆነ በእንስሳት በኩል ብዙ ብርቅዬ ዝርዮች አሉ።