ዓፄ ቴዎፍሎስ
ቴዎፍሎስ፣ ዙፋን ስም ወልደ አምበሳ፣ ከ1700 እስከ 1704 ዓም ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። የቀዳማዊ ዓፄ ኢያሱ ወንድም ነበሩ።
የአጼ ኢያሱ ልጅ ዓፄ ተክለ ሃይማኖት ከተገደሉ በኋላ፣ ቴዎፍሎስን ከደብረ ወህኒ አምጥተዋቸው ንጉሠ ነገሥት ተደረጉ። የተክለ ሃይማኖት ወንድ ልጅ አራት ዓመት ሕጻን ሲሆን የፈረስ አለቃ ዮሐንስና የኢያሱ ንግሥት መለኮታዊት ድጋፍ ነበረለት። ቴዎፍሎስ ግን ቶሎ ብለው ዮሐንስ በአጸ ተክለሃይማኖት ላይ ሤራ ውስጥ ነበር ብለው ከሠውት አሰሩትና ከአገሩ ሰደዱት።.[1]
በአቶ ጄምስ ብሩስ ዘንድ፣ በመጀመርያው የወንድማቸውን የኢያሱ ቂም እንደማይበቅሉ ቢመስልም፣ ይህ ማታለል ነበርና ያው ወገን ከተዝናና በኋላ እርምጃ ወሰዱባቸው። የአረፉት አጼ ተክለ ሃይማኖት አባታቸውን በመግደላቸው ረገሙዋቸው፤ ከዚያም ጀምሮ ነው «እርጉም ተክለሃይማኖት» የተባሉት። ንግሥት መለኮታዊት ስለ ሚናቸውና ሁለት ወንድሞቻቸው ደግሞ ተገደሉ። በብሩስ መሠረት በአንድ ቀን 37 ሰዎች ይሙት በቃ አገኙ።[2] ቴዎፍሎስም የወንድማቸውን የኢያሱ ቅዱስነት አወጁ።
ዘመኑ ሰላማዊ አልሆነም። በ1701-1702 ዓም በአመጽ ነባሕነ ዮሐንስ የተባለው ንጉሠ ነገሥት መሆኑን ዓወጀ። ቴዎፍሎስ ደግሞ «ወልድ ቅብ» የተባለውን ትምህርት ደገፉ። የደብረ ሊባኖስ መኖክሳት ለምንድነው ሲጠይቋቸው፣ «ስለምጠላችሁ ሳይሆን፣ ጎጃም እንድትገዛልኝ ስለ ሆነ ነው» ብለው እንደመለሱላቸው ይባላል።[3]
አጼ ተዎፍሎስ በኣጠያያቂ ሁኔታ አርፈው በቴዳ ተቀበሩ።
ቀዳሚው ዓፄ ተክለ ሃይማኖት |
የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት 1700-1704 ዓም |
ተከታይ ዓፄ ዮስጦስ |
|