Jump to content

ሜሪላንድ

ከውክፔዲያ
ሜሪላንድ ክፍላገር
የሜሪላንድ ባንዲራ የሜሪላንድ ማኅተም
ዋና ከተማ አናፖሊስ
ትልቋ ከተማ ባልቲሞር
አገረ ገዥ ማርቲን ኦማሊ
የመሬት ስፋት 32,160 ካሬ ኪ.ሜ.(ከአገር 42ኛ)
የሕዝብ ብዛት 5,296,486(ከአገር 19ኛ)
ወደ የአሜሪካ ሕብረት

የገባችበት ቀን

April 28,1788 እ.ኤ.ኣ.
ላቲቲዩድ (ኬክሮስ) 37"53'N እስከ 39"43'N
ሎንግቲዩድ (ኬንትሮስ) 75"4'W እስከ 79"33'W
ከፍተኛው ነጥብ 1,024ሜ.
ዝቅተኛው ነጥብ 0ሜ.
አማካኝ የመሬት ከፍታ 105ሜ.
ምዕጻረ ቃል MD
ድረ ገጽ www.maryland.gov


ሜሪላንድ (እንግሊዝኛ፦ Maryland) በአሜሪካ የምትገኝ ስቴት ስትሆን ምዕጻረ ቃሏ MD ወይም Md. ነው። ሜሪላንድ ከአሜሪካ አስራሶስት ጥንታዊ ስቴቶች አንዷ ናት። ከሜሪላንድ ጋር የሚገናኙ ስቴቶች ፔንስልቫኚያቨርጂኚያዌስት ቨርጂኚያ ፣ እና ዴላዌር እያሉ፤ ደግሞ በኮለምቢያ ክልል (ዋሽንግተን ዲ.ሲ.)ና በአትላንቲክ ውቂያኖስ ትወሰናለች። የቼሳፒክ ወሽመጥ ስቴቱን መሃል ለመሃል ይከፍለዋል። የሜሪላንድ ከፍተኛ ቦታ የባክቦን ተራራ ጫፍ ነው። የሜሪላንድ አየር ሁኔታ ከቦታ ቦታ ይለያያል። የምስራቅ ክፍሉ ሞቃታማ በጋና መካከለኛ ክረምት የአየር ሁኔታ ሲኖረው የምዕራብ ክፍሉ ደግሞ መካከለኛ በጋ እና በጣም ቀዝቃዛ ክረምት አለው። የሜሪላንድ ጠቅላላ ምርቶች በ2003 እ.ኤ.ኣ. ወደ 212 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ነው። በዚሁ ዓመት የአንድ ሰው የዓመታዊ ገቢ በኣማካይ 37,446 የአሜሪካን ዶላር ነበር ፣ ከአገሩ 5ኛ። ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ ወታደራዊ ካምፖች እና የሳይንስና የሕክምና ተቋማት በዚሁ ክፍላገር ይገኛሉ። የስቴቱ ዋና ያውሮፕላን ማረፊያ ባልቲሞር-ዋሽንግተን ዓለም አቀፍ ያውሮፕላን ማረፊያ (BWI) ነው። በ1996 የሜሪላንድ ጠቅላላ የህዝብ ብዛት 5,558,058 ነው ተብሎ ይገመታል። ከዚሁ ውስጥም 583,900ቹ ወይም 10.6 በመቶ ሌላ ስቴት ወይም አገር የተወለዱ ነዋሪዎች ናቸው። አብዛኛው ህዝብ የስቴቱ መዓከላዊ ክፍል ውስጥ ይኖራል።

የህዝቡ የዘር ክፍልፋይ

  • 62.1%-ነጭ
  • 27.9%-ጥቁር
  • 4.3%-ላቲን
  • 4.0%-ኤሲያን
  • 0.3%-ቀይ ህንድ
  • 2.0%-ክልስ

የሐይማኖት ክፍልይ

  • ክርስቲያን-82%
    • ፕሮቴስታንት-56%
      • ባፕቲስት-18%
      • ሜቶዲስት-11%
      • ሌላ ፕሮቴስታንት-27%
    • ሮማን ካቶሊክ-23%
    • ሌላ ክሪስቲያን-3%
  • ይሁዳ-3%
  • ሌላ ሐይማኖት-15%

ታዋቂ ከተሞች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በሜሪላንድ ውስጥ የሚገኙ ክልሎች(ካውንቲዎች)

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ካውንቲ የተመሠረተበት ዓ.ም.(እ.ኤ.ኣ.) የመንግስት መቀመጫ
አለገኒ ካውንቲ 1789 ከምበርላንድ
አን አረንዴል ካውንቲ 1650 አናፖሊስ
ባልቲሞር ካውንቲ 1659 ታውሰን
ካልቨርት ካውንቲ 1654 ፕሪንስ ፍሬድሪክ
ካሮላይን ካውንቲ 1773 ዴንተን
ካሮል ካውንቲ 1837 ዌስትሚንስትር
ሲሲል ካውንቲ 1672 ኤልክተን
ቻርልስ ካውንቲ 1658 ላ ፕላታ
ዶርቸስተር ካውንቲ 1668 ኬምበሪጅ
ፍሬደሪክ ካውንቲ 1748 ፍሬደሪክ
ጋሬት ካውንቲ 1872 ኦክላንድ
ሀርፎርድ ካውንቲ 1773 ቤል ኤር
ሀዋርድ ካውንቲ 1851 ኤሊኮት ሲቲ
ኬንት ካውንቲ 1642 ቼስተር ታውን
ሞንትጎመሪ ካውንቲ 1776 ሮክቪል
ፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ 1695 አፐር ማርልቦሮ
ክዊን አን ካውንቲ 1706 ሴንተርቪል
ሴንት ሜሪ ካውንቲ 1637 ለናርድታውን
ሶመርሰት ካውንቲ 1666 ፕሪንስስ አን
ታልቦት ካውንቲ 1662 ኢስተን
ዋሽንግተን ካውንቲ 1776 ሄገርስታውን
ዊኮሚኮ ካውንቲ 1867 ሳሊስበሪ
ዎርስተር ካውንቲ 1742 ስኖው ሂል

ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • ባልቲሞር ኸብሪው ዩኒቨርሲቲ
  • ባልቲሞር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ
  • ካፒቶል ኮሌጅ
  • ቼሳፒክ ኮሌጅ
  • ኮሌጅ ኦፍ ኖትር ዳም ኦፍ ሜሪላንድ
  • ኮለምቢያ ዩኒየን ኮሌጅ
  • ጋውቸር ኮሌጅ
  • ሁድ ኮሌጅ
  • ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ
  • ሎዮላ ኮሌጅ
  • ሜሪላንድ ኢንስትቲዩት ኮሌጅ ኦፍ አርት        
  • ማክዳንኤል ኮሌጅ
  • ሞንትጎምሪ ኮሌጅ
  • ሞርጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ
  • ማውንት ሴንት ሜሪ ዩኒቨርሲቲ
  • ሴንት ጆንሰ ኮሌጅ
  • ሴንት ሜሪ ኮሌጅ ኦፍ ሜሪላንድ
  • ሶውጆርነር-ዳግላስ ኮሌጅ
  • ዩኒፎርምድ ሰርቪስስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዘ ኸልዝ ሳየንስስ
  • ዩናይትድ ስቴትስ ኔቫል አካዳሚ
  • ቦዊ ስቴት ዩኒቨርሲቲ
  • ኮፒን ስቴት ዩኒቨርሲቲ
  • ፍሮስትበርግ ስቴት ዩኒቨርሲቲ
  • ሳሊስበሪ ዩኒቨርሲቲ
  • ታውሰን ዩኒቨርሲቲ
  • ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ባልቲሞር
  • ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሜሪላንድ
  • ዩኒቨርሲቲስ አት ሼዲ ግሮቭ
  • ዋሽንግተን ባይብል ኮሌጅ
  • ዋሽንግተን ኮሌጅ
  • ቪላ ጁሊ ኮሌጅ