Jump to content

ሐውት

ከውክፔዲያ

ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሕ ሖ ሗ



አቡጊዳ ታሪክ

ሐውት ወይም በአነጋገር ሐመረ ሐአቡጊዳ ተራ ስምንተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓንአራማያዕብራይስጥሶርያም ፊደሎች ስምንተኛው ፊደል "ሔት" ይባላል።

ዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል "ሐእ" (ح) ተብሎ በ"አብጃድ" ተራ 8ኛ ነው። "ኀእ" የሚለው አረብኛ ፊደል (ﺥ) ደግሞ ከዚያ ወጣ።

በመጀመርያው (ግዕዝ) ቅርጽ (ሐ) በልሳነ ግዕዝ እንደ ሌሎቹ ፊደላት የ"ኸ" አናባቢ ድምጽ ሆነው ነበር፤ በአማርኛ ግን ድምጹ እንደ አራተኛው (ራብዕ) ቅርጽ (ሓ) አንድላይ ነው።

በአማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ ከሆይ (ሀ) ከኀርም (ኀ) እና ከኻፍ (ኸ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል። ቀድሞ ግን ድምጾቻቸው የተለያዩ ነበሩ።

ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል ቅድመ-ሴማዊ ሣባ ግዕዝ
N24


የሐውት መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የአጥር ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ "ሰፐአት" ነበር። በሌሎች ሊቃውንት ዘንድ ግን የግቢ ወይም የገመድ ሃይሮግሊፍ ነበር

ከነዓን አራማያ ዕብራይስጥ ሶርያ ዓረብኛ
ሐውት ሐውት ח ሐውት ح


የከነዓን "ሔት" እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ "ሔት" የአረብኛም "ሐእ" እና "ኀእ" ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት "ኤታ" ( Η η) አባት ሆነ። እሱም የላቲን አልፋቤት (H h) እና የቂርሎስ አልፋቤት (И и) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ"ሐውት" ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር (ስምንት) ከግሪኩ Η በመወሰዱ እሱም የ"ሐ" ዘመድ ነው።