የውጭ ስብስብ
Appearance
ሁለት ስብስቦች ሊቀናነሱ ይችላሉ። A \ B (ወይም A − B) ማለቱ ማናቸውም በA ውስጥ ኖረው ነገር ግን በ B የማይገኙ አባላት ስብስብ ማለቱ ነው።
በአንድ አንድ ስሌቶች ማናቸውም ስብስቦች የአቃፊያቸው አለም አቀፍ ስብስብ አባል እንደሆኑ ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ። ይህ ሁሉን አቃፊ ስብስብ እንዲህ ይወከላል፡ U ። በዚህ ጊዜ U \ A የ A ውጭ ወይንም የ Aተቃርኖ ይሰኛል።
ምሳሌ:
- {1, 2} \ {ቀይ፣ ነጭ} = {1, 2}.
- {1, 2, አረንጓዴ} \ {ነጭ፣ ቀይ፣ አረንጓዴ} = {1, 2}.
- {1, 2} \ {1, 2} = ∅.
- {1, 2, 3, 4} \ {1, 3} = {2, 4}.
- አለም አቀፉ ስብስብ U የመቁጠሪያ ቁጥሮችን ቢወክል, E ደግሞ ተጋማሽ ቁጥሮችን, O ኢተጋማሽ ቁጥሮችን ቢወክል, E′ = O.
መሰረታዊ የውጭ ስብስብ ጸባዮች:
- A \ B ≠ B \ A.
- A ∪ A′ = U.
- A ∩ A′ = ∅.
- (A′)′ = A.
- A \ A = ∅.
- U′ = ∅ and ∅′ = U.
- A \ B = A ∩ B′.
የAእና የB ሚዛናዊ ውጭ ስብስብ እንዲህ ይተረጎማል።
ለምሳሌ የ {7,8,9,10} እና {9,10,11,12} ሚዛናዊ ውጭ ስብስብ {7,8,11,12} ነው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |